የኢፌዲሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ፣ የኢፌዲሪ ሠራተኛ እና ማህበራዊ ሚኒስቴር እና የኢፌዲሪ ጤና
ሚኒስቴር በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከሚገኘው እና ሪስፖንስ ፐልስ ሆልዲንግስ (PJSC)
ከተሰኘው ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱን ኢትዮጵያን ወክለው የፈረሙት የጤና
ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ‘’ በጤናው ዘርፍ ለተፈጠረው የሥራ ዕድል አመስግነው ለኢትዮጵያውያን
የጤና ባለሞያዎች ከሥራም ባሻገር የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዘመናዊ በሆነ ህክምና የታወቀች
በመሆኗ ዕውቀት እና ልምድ ለማግኘት ይጠቅማል’’ ብለዋል፡፡
ስምምነቱ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ያሻሻለውን የውጭ አገር የሥራ ስምሪት አዋጅ ትከትሎ የተፈፀመ
ሲሆን በየደረጃው ከ200 በላይ የጤና ባለሞያዎችን ባርጀል የህክምና ማዕከልን በመሳሰሉ የተለያዩ
ትልልቅ ሆስፒታሎች ሥራ ለማስጀመር እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የሪስፖንስ ፐልስ ሆልዲንግስ (PJSC)
ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማጆር ቶም ሉዊስ ‘’ለጤና ባለሞያዎቹ የሥራ ዕድል ማመቻቸት ከሥራ ዕድል
ፈጠራ ኮሚሽን፣ ከሠራተኛ እና ማህበራዊ ሚኒስቴር እና ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ ከምንሰራቸው
ሥራዎች መካከል የሚጠቀስ ሲሆን በቅርቡ ሪስፖንስ ፐልስ ሆልዲንግስ (PJSC) በኢትዮጵያ
ቢሮውን ይከፍታል’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሪስፖንስ ፐልስ ሆልዲንግስ (PJSC) በአቡ ዳቢ በጤናው ዘርፍ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ሲሆን
ከ260 በላይ ክሊኒኮች ሲኖሩት በሀገሪቱ ዘመናዊ የግል አምቡላንስ አገልግሎት ተቋም ባለቤት መሆኑን
ገልፍ ኒውስ በዜናው ጠቅሷል፡፡

ያጋሩት