የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ እና ሥራ ዕድልን በተመለከተ ባሳለፍነው ሳምንት ከዓለም ባንክ ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በዚህ ውይይት ላይ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የቴክኒክና ሙያ ስልጠናው በሥራ ገበያው የተቃኘ እንዲሆን እና ለወጣቶችም የሥራ ፈጠራ አስተሳሰብን ለማስረፅ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት አማካኝነት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዓለም ባንክ ትምህርት ዘርፍ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ሳፋ ኤል ኮጋሊ የኢትዮጵያ መንግስት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴርን በማቋቋም ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ትልቅ ኃላፊነት ሰጥቶ በቴክኒክና ሙያው ዘርፍ ጥራትን ለማስጠበቅ እና ብዙ ሥራዎች እንዲፈጠሩ ያደረገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
የሁለቱም ተቋማት አመራሮች የትብብር ሥራቸውን በማጠናከር ለአገሪቱ ዕድገት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡

ያጋሩት