ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የወጣቶችን የሥራ ፈጠራ ሃሳቦች ለማበረታታት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር የሚያከናውነው
የ 2014ዓ.ም የጀነሬሽን አንሊሚትድ ለውጥ አምጪ የወጣቶች ውድድር ይፋ ሆኗል። የውድድሩ ተልዕኮ በዓለማቀፍ
ደረጃ 1.8 ቢሊዮን ወጣቶችን ከተለያዩ ዕድሎች ጋር ማገናኘት መሆኑ ተገልጿል።
በሥነ ስርዓቱ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት አቶ ጥዑመዝጊ በርሔ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር
የአጋርነት እና ፈንድ ዳይሬክተር ወጣቶችን የማገናኘት እና አቅማቸውን የማሳደግ እንቅስቃሴ በቀድሞ ሥራ ዕድል ፈጠራ
ኮሚሽን ተጀምረው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከቀጠሉት አንዱ ሆኖ ይህ ዓለማቀፍ መሆኑ ይለየዋል ብለዋል። 35
በሚጠጉ አገራት መካከል የሚካሄድ፣ በአገራችን 5 ከተሞች ተከናውኖ በ 8 ሳምንታት የሚጠናቀቅ ፣ ሁለት ተወዳዳሪ
ቡድኖችን ለዓለማቀፍ ውድድር የሚያዘጋጅ፣ ለአገራችን ወጣቶች ትልቅ መነቃቃት የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው ወጣት
ሥራ ፈጣሪዎች ዕድሉን እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።
በመክፈቻው ላይ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ተወካይ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ልዩ ሃሳቦቻቸውን አዳብረው
የማኅበረሰባቸውን ችግር በመፍታት ተፅዕኖ ማሳደር እንዲችሉ ድጋፍ በማድረጋችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
ውድድሩ ኢትዮጵያዊ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ዘላቂ የልማት ግቦችን ስኬት ለማፋጠን የሚቀርቡ የፈጠራ ሃሳቦች ላይ
አትኩሮ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ሃሳባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ መነሻ ገንዘብ ይመድባል።
ይህ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተዘጋጀ ውድድር የማመልከቻ መቀበያው ጥር 17 ቀን 2014ዓ.ም ሆኖ የካቲት 1ቀን
2014ዓ.ም ይጠናቀቅና ውድድሩ ይቀጥላል።
ይህንን ውድድር የተለያዩ ዓለማቀፍ ተቋማት የደገፉት ሲሆን ሥራው በፈርስት ኮንሰልት አማካኝነት ይከናወናል።
በኦላይን ለመመዝገብ https://bit.ly/3rQOERQ

ያጋሩት