የስንታየሁ ታሪክ

“ አካሌ ለመታዘዝ አስቸጋሪ በመሆኑ እንደፈለኩ መስራት ባልችልም ሥራዬን ከመክሰም ያዳኑልኝን አመሰግናለሁ ”

ዕድሜዋ 35 ሲሆን ተወልዳ ያደገችው በባህር ዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ ቀበሌ 16 ራስ አገዝ አካባቢ ነው፡፡ እስከ 8ኛ ክፍል ተምራለች፡፡ አሁን የምትኖረው ከወንድሟ ጋር እዚያው ባህርዳር ከተማ ነው፡፡ስንታየሁ በለጠ አሁን የምትሰራውን የሸቀጣሸቀጥ ንግድ ሥራ ከመጀመሯ በፊት በልብስ ሥፌትና ጥልፍ ሥራ ላይ ለረጅም ዓመት ስትሰራ መቆየቷን ነግራናለች ፡፡


ለማንበብ ይጫኑ
የአመለ ወርቅ ታሪክ

“ውሃ እየሸጥን ነበር የምንተዳደረው፤ አሁን ሁለት ሚሊዮን ብር ካፒታል አለኝ”

አመለ ወርቅ ተሬሳ እባላለሁ፡፡የምኖረው በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 07 ልዩ ስሙ ሩዝ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ ባለትዳርና የ7 ልጆች እናት እና የስነ ውበት ባለሙያ ነኝ፡፡ የድርጅቴ ስም ኤሚ ስፓ ይባላል፡፡ ካፒታሌ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ሆኗል፡፡ የምንሰራው ሥራ የወንዶችንና የሴቶችን ውበት መጠበቅ ነው፡፡ በሁለቱም ጾታ ጸጉር ቤት፣ ስፓ፣ ስቲም፣ ማሳጅና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን፡፡


ለማንበብ ይጫኑ
የሀና ታሪክ

“ህልምን እውን ለማድረግ እያንዳንዱን ርቀት መጓዝ- Walk every mile to make yourdream come true!”

የኢንቴሪየር ዲዛይን ሥራ እንደዛሬው በስፋት ባልተለመደበት ጊዜ ከስምንት ዓመታት በፊት ሃና ዮሐንስ ሥራውን
በድፍረት ጀመረች፡፡
ዘርፉ በሥራ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም እራሱን ችሎ እንደትምህርት የማይሰጥ
እንደነበር ሃና ትናገራለች ፡፡


ለማንበብ ይጫኑ
የፍቅርተ ታሪክ

“እናት ሥራ መሥራት ቢኖርባትም ከልጆቿ መራቅ ግን የለባትም!”

“ሴቶች ካሉባቸው ተደራራቢ የቤተሰብ ኃላፊነቶች መካከል ልጅ ማሳደግ አንዱ ነው። ለበርካታ ሴቶች ወደ ሥራ ቦታ ልጆቻቸውን ይዘው መምጣት የማይመች ሁኔታ አለው። ቤት ትተው ለመምጣትም ቀላል አይሆንም። ሴቶችን ባሉበት በሚመቻቸው ቦታ ሆነው እንዲሰሩ አቅማቸውን ማጎልበት የተሻለ ነው። እኔ ራሴ የሦስት ልጆች እናት ነኝ። የራሴን ሥራ ለመሥራት የወሰንኩት ለዲዛይን ካለኝ ፍቅር ባሻገር ለልጆቼ የእናትነት ጊዜዬን እንደፍላጎቴ መስጠት እንዲያስችለኝ ነው።”


ለማንበብ ይጫኑ
የኃብቴ ታሪክ

"በትምህርት ጎበዝ መሆን ብቻውን ሥራ ፈጣሪ ለመሆን አይበቃም!"

“ሥራ ፈጠራ በትምህርት ብቻ የሚገኝ ነገር አይደለም። በቀለም ትምህርት ጎበዝ መሆን ብቻውን የራስ ሥራ ለመጀመር አይበቃም። ጥንካሬና ራዕይ፣ በራስ መተማመንና ለፈተናዎች ሁሉ ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል። ሥራ መፍጠር ለየት ያለ አተያይ ይፈልጋል። በትምህርት ጎበዝ መሆን ብቻውን ሥራ ፈጣሪ ለመሆን አይበቃም። የማህበረሰቡን ችግር ለየት ባለ መረዳት ማየት ያስፈልጋል”


ለማንበብ ይጫኑ
የሜሮን ታሪክ

"ነገሮች የሚሳኩት መውደቅ የማንፈራ ከሆነ ነው! ወጣት በፍፁም ተስፋ መቁረጥ የለበትም!"

"ነገሮች የሚሳኩት መውደቅ የማንፈራ ከሆነ ነው፡፡ በተለይ ወጣት ተስፋ መቁረጥ የለበትም! ጤናም ጉልበትም እውቀትም የሚኖረው በወጣትነት እድሜ ስለሆነ መሮጥ ያለብን ይሄኔ ነው። ብንወድቅም ደግሞ ራሳችንን አንስተን ድጋሜ መሮጥ ነው እንጂ ተስፋ መቁረጥ በፍፁም አያስፈልግም፡፡ በቃ ህይወት ይቀጥላል!"


ለማንበብ ይጫኑ
የዳንኤል ታሪክ

"ስራ ፈጣሪ ማለት በሚቻለው መንገድ ብቻ የሚሄድ ሳይሆን በማይቻለውም ማለፍ የሚችል ነው!"

ስራ ፈጣሪነት ማለት በሚቻለው መንገድ ብቻ ሳይሆን በማይቻለውም ማለፍ መቻል ነው፡፡ በስራ ፈጣሪነት አለም ውጣ ውረዶች በዝተው ተስፋ አስቆራጭ ነገር ቢያጋጥም እንኳን ዋናው ነገር አላማን ማሰብ እና ተስፋ አለመቁረጥ ተገቢ ነው፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ ደግሞ እንኳን ስንጀምር ይቅርና አሁንም ሁሉም ነገር ሙሉ አይደለም፡፡ በስራ ፈጣሪነት አለም ውስጥ ሁሌም ውጣ ውረድ እና ፈተና አለ፡፡


ለማንበብ ይጫኑ
የማህሌት ታሪክ

"የሚያልሙትን ነገር ካልሞከሩ በስተቀር መሳካት አለመሳካቱ አይታወቅም ፡፡"

ሰው የትኛውንም ያህል ተሰጥኦ ቢኖረው ጠንካራ ሰራተኛ ካልሆነ እንዲሁም ወደሚፈልገው ህልም የሚወስደውን መንገድ ተነስቶ ካልጀመረ ስኬታማ አይሆንም፡፡ ስኬት ደግሞ ግዴታ ትልቅ ገንዘብ ማግኘት አልያም ትልቅ ቦታ ላይ መቀመጥ ብቻ አይደለም! ወደ ህልማችን የሚወስደንን መንገድ ተነስተን ጀመርን ማለት ስኬታማ ለስኬታችን በር እየከፈትን ነው ማለት ነው።


ለማንበብ ይጫኑ
የአዛሪያ ታሪክ

"አላማችን ዓለም ስለአፍሪካ የሚሰጠውን የወረደ ግምት መቀየር ነው!"

ዓለም ስለ አፍሪካ በተለይም ደግሞ ስለ ምስራቅ አፍሪካ የሚሰጠው የወረደ ግምት እኔንና ጓደኛዬን ጃዋድን ዘወትር የሚያሳስበን ጉዳይ ነው። የዛሬ አስር አመት ገደማ ለንደን በሚገኘው ቤታችን ቁጭ ብለን ስለዚሁ ጉዳይ እንደሁልጊዜው በምንወያይበት ጊዜ ይህን የተሳሳተ ግምት ለማስቀየር የሚያስችለንን የስራ ሀሳብ አፈለቅን፡፡ እሱም በአፍሪካውያን ከአፍሪካ ተመርተው ለዓለም ገበያ የሚወጡ ቅንጡ ጫማዎችን መስራት ነበር፡፡


ለማንበብ ይጫኑ
የጃኔት ታሪክ

“ለጀማሪ ስራ ፈጣሪነት የአዕምሮ ዝግጁነት ያስፈልጋል !”

የስራ ፈጣሪነት ጉዞ በጣም ፈታኝ እንደሆነ አይቼዋለሁ፡፡ ቀላል መንገድ አይደለም! በተለይ ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ማለት የምፈልገው ነገር የአዕምሮ ዝግጁነት ያስፈልጋል ነው፡፡ ምክንያቱም ጀማሪ ስራ ፈጣሪ ሲኮን የሚፈለገው ነገር ሁሉ ተሟልቶ አይኖርም፡፡ ብዙ የሚገድቡ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ የቢዝነሱ ፈጣሪም፣ ሽያጭ ባለሞያም ፣ የፋይናንስ ባለሞያም መሆን ሊያስፈልግ ይችላል የስራ ፈጣሪነት መንገድ ቀላል እንዳልሆነ እና የአዕምሮ ዝግጁነት እንደሚያስፈልግ መታወቅ አለበት፡፡ማንም ሰው በፈጠራ ችሎታው ወይም ልዩ በመሆኑ ማፈርም ሆነ ከመስራት ወደ ኋላ መቅረት የለበትም፡፡


ለማንበብ ይጫኑ
የሰምሃል ታሪክ

“በእኛ ሀገር ሁኔታ ወጣትና ሴት ተኾኖ ስራ ፈጣሪነት ቀላል አይደለም”

የማምረቻ ኢንዱስትሪው በብዛት በወንዶች የተያዘ ነው፡፡ ወጣት ሲኾን ደግሞ እንደልብ ከባንክ ብድር የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በዘርፉ ቀድሞ የገባ/ች ወይም በስራው በደምብ ልምድ ያዳበረ/ች መካሪ ከሌለ ጉዞው የበለጠ ፈታኝ ይሆናል፡፡ የእኛ ድርጅት ከአረብ ሀገር የተመለሱና በተለያዩ የሴቶች ማህበራት ስር ባሉ መጠለያዎች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን በመውሰድ አሰልጥኖ ይቀጥራል፡፡ እስካሁን ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራን ነው። ከሰራተኞቻችን 80% ሴቶች ሲሆኑ ከእነዚህ 20% ልጆቻቸውን ያለአባት የሚያሳድጉ እናቶች ናቸው፡፡ እንደ ሴትነቴ ብዙ ሴቶችን መጥቀም እችላለሁ ብዬ አምናለሁ ፡፡


ለማንበብ ይጫኑ