ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ፣ በሠራተኛ ዘርፍ እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች
ከክልል አመራሮች ጋር ያለፉት ስድስት ወራትን የሥራ አፈፃፀም አስመልክቶ ሲያካሄድ የቆየውን ውይይት አጠናቋል፡፡
በማጠቃለያው ላይ የሥራ መመሪያ የሰጡት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የክልሎችን ሪፖርት
በማዳመጥ የተሰነዘሩ አስተያየት እና ጥያቄዎችን ተቀብለው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በሥራ ፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኒክና ሙያ ጉዳዮች የውጭ አገር ሥራ ስምሪት፣ የኢንዱስትሪ ሰላም እና የሙያ
ደህንነት፣የተረጋገጠ መረጃ ማደራጀት፣ በግል የስልጠና ተቋማት ላይ የሚታዩ ችግሮች፣ የዚህ ዓመት የሰልጣኞች የቅበላ
ዝግጅት እና ሌሎችም ጉዳዮች ተነስተው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ለተነሱት ዝርዝር ጉዳዮች ማብራሪያ የሰጡት ክብርት ሙፈሪሃት ሦስቱም መሠረታዊ ዘርፎች ላይ ሚዛን ሰጥተን
ተገቢውን ትስስር ፈጥረን መሄድ ከቻልን የተሰጠንን ተልዕኮ ማሳካት እንችላለን ያሉ ሲሆን ጉልበት እና ካፒታልን
አቀናጅቶ ክህሎት ያለው ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት የኢንዱስትሪ ሰላምን በማሳካት የኢንቨስትመንት አቅማችንን ከፍ
ያደርጋል ብለዋል፡፡ ክህሎት እና ብቃት ያለው ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ዘላቂ
የሥራ ዕድል በመፍጠር ለኢኮኖሚው መሠረት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ስልጠና ለመስጠት የቅድሚያ ቅድሚያ በተሰጣቸው ግብርና፣ ማዕድን፣
ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም ፣ትምህርት፣ መስኖ እና አይ.ሲ.ቲ ዘርፎች ትኩረት በመስጠት እና የተጀመረውን ውይይት
በማጠናከር በዙ ሰው ሊሰማራባቸው የሚችሉ የአካባቢን ፀጋ የለዩ የሥራ ዘርፎች ላይ እንደሚሠራ ገልፀዋል፡፡
በአማራ እና አፋር በሔራዊ ክልሎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ፈጣን አማራጮችን እንዲመለከቱ በመደገፍ
ሁሉም ክልል እጁ ላይ ካለው ሀብት ጀምሮ እንዴት ደጋፍ ማድረግ እንዳለበት ተወያይቶ ፈጣን ምላሽ መስጠት አለበት ሲሉ
አሳስበዋል፡፡ በፌደራል ደረጃ መደረግ ያለበትን ድጋፍ በጥናቱ መሠረት ይከናወናል ብለዋል፡፡

ያጋሩት