የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የጠ/ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ዳያስፖራዎችን ከጀማሪ ሥራ
ፈጣሪዎች ጋር የሚያገናኝ መድረክ አካሂዷል።
በወዳጅነት አደባባይ ሥነ ስርዓቱ ሲካሄድ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ፣ ኢንቨስተሮች እና ከተለያዩ አገራት የመጡ
ዳያስፖራዎች ተገኝተዋል።
በክብር እንግድነት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል
ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎችን ማበረታታት እና ስራቸው እንዲቀጥል ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የተከበረች እና የታፈረች አገር እንድትሆን ኢኮኖሚን መገንባት የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በሥራ ፈጠራ ዘርፍ
የጀመርናቸውን ተግባራት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የዕድገት ፕሮግራም መሪ እና የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ በርናንድ ሎሬንዶ በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጀማሪ
ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት የጀመራቸው ከግብ እንዲደርሱ የሁሉንም ትብብር እንደሚጠይቅ አስታውሰው በውጭ
የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዚህ እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።
ፕሮግራሙ ሥራ ፈጣሪዎችን ለማስተሳሰር ያለመ እንደመሆኑ ዳያስፖራዎች ፣ ክቡራን ሚኒስትሮች እና ከተለያዩ ተቋማት
የተገኙ እንግዶች የወጣቶቹን ሥራዎች ጎብኝተዋል።

ያጋሩት