የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር ዋስትና ፕሮግራም

ይህ ፕሮግራም ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍና በፈርስት ኮንሰልት ድጋፍ የሚተገበር በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በሚያጋጥመው የምጣኔ ሃብት ቀውስ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና አዳዲስ ስራ ጀማሪዎችን የሚደግፍ የአደጋ ጊዜ መርሃ ግብር ነው ፡፡ ይህ ፕሮግራም ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ለኮቪድ19 ጫና መልሶ ማገገሚያና መቋቋሚያ ፕሮጀክት በተደረገ የ 24.8 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድርጅቶቻቸውን እንዳይዘጉ፣ ሰራተኞቻቸውን እንዳያሰናብቱና በአሁኑ ወቅት ያለውን ሁኔታ ያገናዘቡ የፈጠራ ስራዎችን እንዲሰሩ የሚያበረታታ ነው።

 

ማዕከሉ ከባንኮች ፣ ማይክሮ ፋይናንስ እና ቢዝነስ ልማት አገልግሎቶች ጋር በመሆን በቋሚም ሆነ ጊዜያዊ ስራ ላይ ለተሰማሩ ብቁ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚደረገውን የገንዘብ ድጋፍ በመከታተል በመከታተልና ሂደቱን በማስተባበር በጋር ይሰራሉ። የሚደረገውም የገንዘብ ድጋፍ መጠን እንደ ኢንተርፕራይዞቹና ስራዎቹ አይነትና ፍላጎት የሚለያይ ይሆናል።

 

በአፈጻጸም ሂደቱ ላይ የሚሳተፉ አጋዥ አካላትን ከተለዩና ከታወቁ በኋላ ለብድር ዋስትናው ብቁ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችን ግልጽ በሆነ መስፈርት በመወዳደር ተሳታፊ ይሆናሉ።

 

ድህረ ገጽ

ቢዝነስ ኢመርጀንሲ ዩኒት (ቢኢዩ)

ቢዝነስ ኢመርጀንሲ ዩኒት (BEU) የኮቪድ 19 ስርጭት በጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሥራ ላይ የሚያሳድረውን ከፍተኛ ጫና ለመቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት ሲሆን ኢንተርፕራይዞቹ ላሉባቸው ጊዜ የማይሰጡ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ (Emergency Response) ለመስጠት እንዲሁም ጫናው ካሳደረባቸው ተጽዕኖ ማገገም እንዲችሉ (Recovery) ለድጋፍ ለማድረግ የተጀመረ ፕሮጀክት ነው።

 

አፋጣኝ እገዛና ምላሽ ለመስጠት የተቀረጸው ይህ ፕሮግራም ከፍተኛ ጫናው በበረታባቸው ዘርፎች የሠራተኛ (የሰው ኃብት) ቅነሳና የምርት መቀነስ እንዳይከሰት ለማገዝ ያለመ ነው። በመደበኛና በኢ-መደበኛ የስራ መስኮች የተሰማሩ በተለይም ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የማሕበረሰብ ክፍሎች የሚያስተዳድሯቸው ድርጅቶች በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት በሚከሰተው ጫና ተጽዕኖ ውስጥ እንዳይወድቁም ከለላ የሚሰጥ ነው። የመልሶ ማቋቋምና ማገገሚያ ፕሮግራሙ ደግሞ ቢዝነሶቹ በምርት፣ በቅጥርና በኤክስፖርት ላይ ከደረሰባቸው ጫና በፍጥነት አገግመው ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው እንዲመለሱ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ የሚያመቻች ነው።

 

የዚህ ፕሮግራም ትግበራ በመጀመሪያው ዙር ከዩኤንዲፒ በተገኘ የ 4.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የሚጀመር ሲሆን በቀጣይም ከመንግስት፣ ከአውሮፓ ህብረት፣ ከፈረንሳይ መንግስትና ከሌሎችን ዓለም አቀፍ አጋር አካላት በሚደረጉ ድጋፎች የሚቀጥል ይሆናል።

 

ድህረ ገጽ

የኮሚሽኑ ዜና-መጽሄት

የኮሚሽኑን ዜና-መጽሄት ለማግኘት እዚህ ይመዝገቡ