የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሚሰሯቸውን ስራዎች
በጋራ አቅደው መስራት እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።
" እንደ አገር በሥራ ባህል በኩል የሚታየውን ሥር የሰደደ የአስተሳሰብ ችግር ለመፍታት በትኩረት እንሰራለን " ያሉት
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት፤ በጋራና በመተባበር መንፈስ በመሥራት የህዝባችንን ችግር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆን
ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስትሯ ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች
በሚያሳኳቸው ግቦች የጋራ የሚያደርጓቸው ጉዳዮች ታላላቅ በመሆናቸው በመቀራረብና በመናበብ ክፍተቶችን እየሞሉ
መሥራት ይገባቸዋል፡፡
በዚሁ ውይይት ወቅትም በከተሞች የስልጠናና የሥራ ክህሎት እንዲሁም ግዙፍ የሰው ኃይል በሚያንቀሳቅሰው
የኮንትራክሽን ዘርፍ ያለውን የስልጠና ፍላጎት በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በቀጣይም በሚኒስትሮችና በቴክኒክ ባለሙያዎች ደረጃ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችሉ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡

ያጋሩት