በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ስር የተዋሀዱ እና ተጠሪ ተቋማትን አሠራር ለማቀናጀት ከ80 በላይ አባላት ያሉት 11 ቡደኖች ተዋቅረው ሲያከናውኑት የነበረው ጥናት እና የሰነድ ዝግጅት ለአመራሩ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የተሠራው ሥራ ትልቅ ውጤት የተገኘበት እና ወደፊት ሊጎለብት የሚችል መሆኑን ጠቅሰው ባለሞያዎቹ ተግተው ዕውቀታቸውን ሳይሰስቱ ባጭር ጊዜ በመደጋገፍ እና በባለቤትነት ስሜት በመሥራታቸው አመስግነዋል፡፡

የዕቅድ ክለሳ እና ዝግጅት ፣ የፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ፣ፐሮጀክት አመራር እና አጋርነት ፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን እና ተቋማዊ ስርዓት ግንባታ ፣ የኮሙኒኬሽን ፣መልካም አስተዳደር እና ስነምግባር፣ ህግ እና ፖሊሲ ዝግጅት፣ የሰው ሃብት አስተዳደር እና ልማት፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ እና አንተርፐርነርሺፕ ኢንስቲቲዩቶች እንዲሁም የሥራ ገበያ መርጃ ስርዓት ግንባታ ጥናት የተደረገባቸው እና ሰነዶች የቀረቡባቸው ናቸው፡፡

በየቡድኑ የተሰባሰቡ አባላቱም የተቋሙን አደረጃጀት ከመቅረፅ ጀምሮ ስትራቴጂክ ዕቅዶችን እና የዓመት እና የ100 ቀናት ዕቅድ አዘጋጅተዋል ፡፡

ያጋሩት