በፍሪላንሲንግ፣ አውትሶርሲንግና ጊግ ዘርፎች ላይ የግሉን ዘርፍ በንቃት ያሳተፈ የፍሮግ ግብረሀይል (FROG፡
Freelancing, Outsourcing, Gig Taskforce) ተቋቁሞ ባለፈው አንድ ዓመት የሠራቸውን ሥራዎች የሚገመግም
ውይይት ተካሂዷል፡፡በዲጂታል ኢኮኖሚው የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየው እና በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ዕድገት
ፕሮግራም ሥር የሚገኘው ፍሮግ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ስነ ምህዳር ለሥራ ፈጠራ ምቹ ለማድረግና ኢኮኖሚያዊ
ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የያዛቸውን 17 የግል ዘርፍ ግብርሃይል ወደ 30 በማስፋት በቀጣይ የተለያዩ ተግባራትን በጋራ
ለማከናወን መታቀዱን አቶ በርናነድ ሎሬንዶ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዕድገት ፕሮግራም መሪ ተናግረዋል፡፡
በፍሮግ ግብረ ሃይል ሲከናወኑ የነበሩ ተግባራት፤ የተፈጠሩ የሥራ ዕድሎችና በቀጣይ በፕሮግራሙ ሊሰሩ የታሰቡ ዝርዝር
ተግባራት ለተሳታፊዎች በአቶ ዳዊት ሙሉጌታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ቀርበዋል፡፡
በቀጣይ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የግሉን ዘርፍ በንቃት በማሳተፍ የ5 ዓመት የዲጂታል አንተርፕርነርሺፕ ስትራቴጂ ዕቅድን
ተግባራዊ በማድረግ በዲጂታል ዘርፍ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሥራ ዕድሎች እንዲፈጠሩ ለማስቻል የበኩሉን አስተዋፆ
ለማበርከት ዝግጁ መሆኑን የገለፁት አቶ ለዑል ዮሃንስ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሥራ ፤ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ
ተወካይ ከተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ለአብነት ብሔራዊ ዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ፤ የጀማሪ የንግድ ድርጅቶች አዋጅ እና
አንተርፕረነርሺፕ ፈንድ ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ውጤታማ የሚያደረጋቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ለማድረግና የእርስ በእርስ ትስስር ለማጠከር በተደረገው ውይይት የፍሮግ ማህበረሰብ
አባላት፤ ስነ ምህዳሩ ላይ በንቃት የሚሳተፉ ከግሉ ዘርፍ የተወከሉ ፤ ከመንግስት ተቋማት፤ አጋር ድርጅቶች የመጡ
እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ መረጃ በማጋራት ፍሮግን ስለ ማስቻል እና በፍሮግ ኢኮኖሚ ላይ የፓናል ውይይት
ተደርጓል፡፡

ያጋሩት