የኢ.ፌ.ድ.ሪ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ፣ ዜንይሲስ ቴክኖሎጂስና ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ የቅጥር መረጃዎችን በማጠናቀር በመረጃ የተደገፉ ውሳኔዎችን ለማድረግ የሚያግዝ አዲስ የዲጂታል ፕሮ ክት ለመ መር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። ይህ ስምምነት ኮሚሽኑ እ.ኤ.አ በ 2030 ዓ.ም 20ሚሊዮን ዘለቄታ ያላቸው የስራ ዕድሎች መፈጠርን ለማመቻቸት ላቀደው ዕቅድ መቀላጠፍ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ነው።

ፕሮጀክቱ ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ከተባለው ፋውንዴሽን በተደረገ የ500,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለሠራተኛ ገበያ መረጃ ስርዓት ማደራጃ የሚሆን መሰረት ይጥላል። የዚህ መረጃ ስርዓት መደራ ት የሥራ ስምሪት መረጃዎችን ከተለያዩ ምንጮች በማሰባሰብ ፣ ለፖሊሲ እና ስትራቴጂ አወጣጥ እንዲሁም አሠሪዎች ፣ የሥራ ፈላጊዎች እና የስራ ስምሪት ኤጀንሲዎችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በስራ ፈጠራ ሥነ ምህዳር በቅንጅት እንዲሰሩ ይረዳል።

በስድስት ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ የታቀደው ይህ ፕሮጀክት መጀመሩን የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ኤፍሬም ተክሌ፣ የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አዴቶኩንቦ ኦሺን እንዲሁም የዜንይሲስ ቴክኖሎጂ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ካሳ በጋራ አብስረዋል።

ውሳኔ ሰጭዎችና ተንታኞች በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔን ለማድረግ እንዲችሉ አስተማማኝ እና ወቅታዊ መረጃን የሚያስገኙ ትላልቅ የትንታኔና መረጃ ሰጪ ቴክኖሎጂዎች በዓለም ዙሪያ ጥቅም ላይ ውለዋል ፡፡ በአብዛኛው መንግስታትና ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች በቴክኖሎጂ ፣ በመረጃ ልሂቃዊነትና በቃላት አጠቃቀሞች እርስ በእርስ የሚለያዩትን የመረጃ ስርዓቶችን ማዋሃድ ፈታኝ ሥራ ይሆንባቸዋል ፡፡

ይህ አዲስ ሽርክና እና ፕሮ ክት ኮሚሽኑ የአገሪቱን የሥራ ስምሪት መረጃ ሥርዓት ከሌላው ዓለም ጋር ተስተካካይ እንዲሆን ስትራቴጂካዊ የፖሊሲ ውሳኔዎችን በማሻሻል ፣ የሥራ ፈጠራ ተነሳሽነትን ለማመቻቸት እና ግልፅነትና ተጠያቂነትን ያለው አሰራርን ለመዘርጋት የሚያስፈልገውን ቴክኖሎጂ እና እውቀት እንዲያጠናክር የሚያግዝ ነው። ይህ ፕሮጀክት ኮሚሽኑ አሉ የተባሉና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የስራ ፈጠራን ለማፋጠን በተዘጋጀበት ወቅት ላይ የተገኘ መልካም አጋጣሚም ነው።

ያጋሩት