ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 29 የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን መሠረት በማድረግ ለአንድ ዓመት ያህል ሲዘጋጅ የቆየው
ጥናት የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ዴቪድ እና ሉሲ ፓካርድ ፋውንዴሽን እንዲሁም ቢቢሲ ሚዲያ አክሽን በጋራ
በመተባበር አራት ክልሎችን እንደ ናሙና በመውሰድ ገጠር እና ከተማን አካቶ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ጥናቱን ይፋ ያደረጉት በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ
ንጉሡ ጥላሁን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአምስት አመቱ ስትራቴጂክ ዕቅዱ ላይ የሰው ሀብት ልማትን ትልቅ ትኩረት
እንደሰጠው አንስተው ይፋ የሆነው ስትራቴጂ የዕቅዱ አካል ሆኖ ወጣቶችን ማነቃቃት ፣አቅማቸውን መገንባት
እንዲሁም የህይወት እና የሥራ ምርጫቸው የተሻለ እንዲሆን የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ሥራዎችን በመስራት በስነ ባህሪ
ላይ ለውጥ ማመጣት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ ይፋ የሆነው ስትራቴጂ ወጣቶች መረጃ እንዲኖራቸው፣ የሰለጠኑ እና
በተለያዩ አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉ እንዲሆኑ እንደሚያግዝ በመግለፅ ግቡ የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግ
ከአጋር አካላት ጋር በመሆን የወጣቶች ስነ ባህሪ ላይ በስፋት መስራት ነው ብለዋል፡፡
በዴቪድ እና ሉሲ ፓካርድ ፋውንዴሽን አማካሪ የሆኑት የምስራች በላይነህ ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር
የተዘጋጅው ስትራቴጂክ ጥናት የኢትዮጵያ ወጣቶች ለሥራ እና ጤናማ ህይወት እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን ያመላከተ
መሆኑን ጠቅሰው በሥራ፣ በትምህርት ፣ ስነ ተዋልዶ ጤና እና ተሳታፊነት ላይ የጠቆማቸውን ችግሮች ለመፍታት
ስትራቴጂውን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
የቢቢሲ ሚዲያ አክሽን የኢትዮጵያ ተወካይ ሚያን መሀመድ ጁኔድ በበኩላቸው በየዓመቱ ሁለት ሚሊዮን ወጣቶች
ወደሥራው ዓለም ለሚቀላቀሉባት ኢትዮጵያ ስነ ባህሪ ላይ የሚሰሩ ስራዎች ላይ አትኩሮ ጥናት ማድረግ የተሻለ ውጤት
እንደሚያስገኝ በማስገንዘብ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሚዲያዎችን በመጠቀም ወጣቶች ላይ ለሚሰራው ሥራ እና a
ክቡር በከር ሻሌ (ዶ/ር)
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
የዓለም ባንክ ፕሮጀክቶች እና የኢትዮጵያ መንግስት የፋይናንስ አፈፃፀም የጋራ ግምገማ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ፕሮጀክት
(East Africa Skills for Transformation and Regional Integration Project-EASTRIP) የሥራ አፈፃፀም
የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የዓለም ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡
ሪፖርቱን ያቀረቡት በኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ቃልኪዳን ታደሰ እንደገለጹት ለፕሮጀክቱ ከተያዘው አጠቃላይ በጀት 70
በመቶ የሚሆነው በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ የልህቀት ማዕከላትን ለመገንባት የሚውል ነው፡፡
በእስካሁኑ ሂደትም በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገነቡት ሰባት የልህቀት ማዕከላት መካከል የስድስቱ ማዕከላት የዲዛይን ስራ
ተጠናቆ ግንባታውን የሚያከናውኑ አካላትን ለመለየት የሚያስችል የጨረታ ሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ክቡር በከር ሻሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፕሮጀክቱ
በትምህርትና ሥልጠናው ዘርፍ ጥራትን ከማረጋገጥ እና በቀጠናው ያለውን ትስስር ከማሳለጥ አኳያ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ
መሆኑን ገልፀው ከፋይናንስ እና ከምትክ ቦታ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ፕሮጀክቱ የገጠሙትን ተግዳሮቶች በቀጣይ ለማስተካከል
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ተቀራርቦ ይሰራል ብለዋል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ትስስር ፕሮጀክት ዓላማው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች ተደራሽነትን
ማሳደግ፣ ጥራትን ማሻሻል እና ቀጠናዊ ትስስርን ማሳለጥ ሲሆን ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሦስት የምስራቅ አፍሪካ
አገራት በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በመተግበር ላይ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት 16 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ
የልህቀት ማዕከላትን በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 7ቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት
ናቸው፡፡
ለጥናቱ
ተነሳሽነት አመስግነዋል፡፡
ጥናቱ በአገራችን ያሉ ለወጣቶች ከሥራ አመለካከት ጋር የተገናኙ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ለመለወጥ መነሻ የሆኑ ግኝቶችን
ማካተቱን በመርሐ ግብሩ ላይ ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ዓለማቀፍ ተቋማት የተገኙ ተሳታፊዎች
ተናግረዋል፡፡