የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማት


ለጀማሪዎች የመነሻ የገንዘብ ድጋፍ የሚሠጡ ድርጅቶች

ሪኒው

ሪኒው በታዳሽ ሃይል፣ ግብርና ውጤቶች ማቀነባባር፣ አምራችና ጤናን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የመዋዕለ ነዋይ ፈሰስ ያደርጋል፡፡

ድርጅቱ ለማስፋፊያ ከ300 ሺ - 3ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከፍተኛ የማደግ አቅም ላላቸው የአገር ውስጥ ድርጅቶች የእንቨስትመንት የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል፡፡ መነሻ የገንዘብ ድጋፍ የተሰጣቸዉ ድርጅቶች ከ3-7 ዓ መት ውስጥ ራሳቸውን ከቻሉ በኋላ የድጋፍ አቅራቢውን ድርጅት የባለቤትነት ድርሻ እንዲገዙ ተደርጎ ሪኒው የባለቤትነት ድርሳን በሙሉ በሙሉ ያስረክባል፡፡
ድረ-ገፅ

ግሮውዝ አፍሪካ

ለጀማሪ ድርጅቶች የስራ ፈጠራ፣ የንግር ስራ ማበልፀጊያ፣ የአመራር ስልጠና እና የመነሻ የገንዘብ ድጋፍ ያቀርባል፡፡ የጀማሪዎችን እድገት ማፋጠን፣ የአገር ውስጥና አለምዓቀፍ ኩባኒያዎች አፍሪካ ውስጥ የሚሰሩትን ስራ እንዲያስፋፉ ድጋፍ መስጠት የዚህ ድርጅት ተልዕኮ ነው፡፡
ድረ-ገፅ

ኖቫስታር ቬንቸርስ

ኖቫስተር ከፍተኛ ተስጥኦ ያላቸውን የቀጣይ ትውልድ አፍሪካዊ ስራ ፈጣሪዎችን በማፈላለግ ለአፍሪካ ህዝብ አትራፊ አገልግሎት እንዲሰጡ አዳዲስ የንግድ አሠራር ስርዓቶችን እንዲያዘጋጁ እና እንዲከውኑ ይደግፋል፡፡

ድረ-ገፅ

ኢግናይት ኢንቨስትመንት

የኢንተርፕሬነርሽፕ፣ ቢዝነስ ማበልፀግ እና የአመራር ስልጠና ይሰጣል፤ ለጀማሪ ድርጅቶች የመነሻ ካፒታል ድጋፍ ያቀርባል፡፡ የጀማሪዎችን እድገት ማፋጠን ፣ የሀገር ውስጥና አለምቀፍ ኩባኒያዎች በአፍሪካ ውስጥ የሚሠሩትን ሥራ እንዲያስፋፉ መደገፍ የዚህ ድርጅት ተልዕኮ ነው፡፡
ድረ-ገፅ