ውድድር


በቶታል ኢትዮጵያ ~ የአመቱ የጅማሮ ንግድ ስራ ተሸላሚ

የጅማሮ ንግድ ስራ ውድድር በአለም አቀፍ ደረጃ በ60 አገሮች ይደረጋል ፡፡ ይህ ውድድር እያንዳንዱ የፈጠራ ሃሳብ ያለው ወጣት የስራ ፈጣሪዎች ወይም አገራቸው ውስጥ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ሃሳብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በእያንዳንዱ አገር ውስጥ የሚገኙ የአከባቢ ዳኞች የገንዘብና የስልጠና ድጋፍ የሚያገኙትን ሶስት ፕሮጀከቶችን ይመርጣሉ፡፡

ድረ-ገፅ

ሶልቭ አይቲ የፈጠራ ሽልማት

በቅርቡ የተቋቋመው አገር አቀፍ የፈጠራ ውድድር ከ18-30 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ትኩረት ያደረገ ፈጠራን እና የስራ ፈጠራን ለማበረታታት ነው፡፡

ተወዳዳሪዎች በሞባይል አፕልኬሽንና በሃርድዌር አማካኝነት በማህበረሰባቸው ውስጥ ያለውን ቁልፍ ችግሮች ይፈታል ብለው ያመኑባቸውን ምርቶች ለማጎልበት ለ9 ወራት ያህል መስራት አለባቸው ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዘጠኝ በክልል የተቋቋሙ ማዕከላትና በሁለት የከተማ አስተዳደር ተቋማት የምርት ማጎልበት የንግድ ስራ እና የገበያ ስልጠና ይሰጣል። የክልል ደረጃ አሸናፊዎች ለብሔራዊ ዙር በማለፍ ለሳምንት በሚቆይ ውድድር የኢንዱስትሪ ባለሞያ በሆኑ ዳኞች ፊት ይቀርባሉ። በ2018 እ.ኤ.አ የመጀመሪያ ሽልማት በኢትዮጲያ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ድጋፍ ተደርጎል። በመጀመሪያው ዙር ውድድር ከ 1600 በላይ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ስራ ፈጣሪዎች ተሳትፈዋል። ወደ 85 አዲስና ለገበያ የሚቀርቡ የቴክኖሎጂ ምርቶችና አገልግሎቶች በመሻገር ለ3 የገንዘብ ተሸላሚ አሸናፊዎች የስራ ፈጣራቸው እንዲተገበር የገንዘብ ድጋፍ ይቀበላሉ፡፡

ድረ-ገፅ

በሳይንስ ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ሽልማት

የመጀመርያውን የማጣሪያ ደረጃ ካለፈ በሗላ 200 ቡድኖች ለመጨረሻውን ዙር ጥረት ይደረጋሉ። የተመረጡ 50 ተወዳዳሪዎች በዓለም አቀፍ ባልሞያዎች ዘመናዊ የአሰራር አተገባበር ስልጠና ያገኛሉ። ምርጥ አስር ፕሮጆክቶች በቻይና በቪንዝኔን ከተማ የጅምላ ማምረት እድል ያገኛሉ።

ድረ-ገፅ

በአፍሪካ ልማት ባንክ የውድድር ሽልማት

በወጣት የሥራ ፈጣሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ስር ባንኩ በየአመቱ ለ20 ምርጥ የአፍሪካ ጥ.አ. ድርጅቶችን ወይም በወጣቶች የሚመራ የጅምር ንግድ ስራዎችን ይሸልማል፡፡

ድረ-ገፅ

ወጣት ወንድና ሴት ስራ ፈጣሪዎች ልማት ማዕከል

የአለም አቀፍ የስራ ፈጠራ ሳምንት አካል የሆነው የስራ ፈጠራ ማጎልበቻ ማዕከል 3 ምርጥ ስራ ፈጣሪዎችን ይሸልማል፡፡

ድረ-ገፅ

ስለሽ አለም አቀፍ ተፅእኖ ፈጠራን የማሻሻል ውድድር

ስለሽ 2500 በላይ ጅማሮ ስራዎችና 1200 ኢንቨስተር ጋር የሚደረግ አመታዊ ውድድር ነው፡፡
ከኢትዮጲያ የመጀመሪያ ~ ኢትዮጲያዊ አሸናፊ ስለገበያ ኔት ቴክኖሎጂስ መስራች ክርስቲያን ተስፋዬ ያንብቡ። ከ1400 አለም አቀፍ አመልካቾች መካከል ተመርጦ ገበያኔት ቴክኖሎጂስ የ5ሺ ዩሮ ዋና አሸናፊ ሆኗል፡፡

ድረ-ገፅ

የአመቱ የማህበራዊ ስራ ፈጣሪዎች

ለማህበራዊ ስራ ፈጣሪዎች በሽዋብ ፋውንዴሽን የሚዘጋጅ ሲሆን ሽልማቱ ለማህበራዊና አካባቢያዊ ችግሮችን ለመፍታት ቀዳሚ የሆኑ ዋና ዋና መሪ ድርጅቶችን ለማበረታታት የተነደፈ ነው። በ2018 እ.ኤ.አ ከኢትዮጲያ የመጀመሪያ አሸናፊ ማን እንደሆነች ያንብቡ፡፡

ብርክታዊት ጥጋቡ ትባላለች የዊዝ ኪድስ ወርክሾፕ መስራች ስትሆን የቴሌቪዥን ሪዲዮ እና የህትመት መንገዶችን በመጠቀም በህፃናት ትምህርትና በፃታ እኩልነት ላይ በማተኮር በሀገራዊ ቋንቋዎች ትምህርታዊ መልዕክት አሰራጭታለች።

ድረ-ገፅ

የቴሌቪዥን ሾው

የኢትዮጲያ ቴክኖቪዥን ንግድ ስራ ውድድር አዲስ የቴሌቪዥን ዝግጅት ሲሆን ሴቶችን የቴክኖሎጂ ስራ ፈጣሪና መሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ችሎታ የሚያገኙበትን እድል ያቀርባል፡፡

ድረ-ገፅ

ችግኝ ጦቢያ የንግድ ሥራ ውድድር (ፋና ቲቪ)

ብቶንተር መልቲ ሚዲያ እና ፋና ቲቪ የሚዘጋጀው አገር አቀፍ ውድድር በሁለቱም በሀሳብ ደረጃ ወይም በስራ ላይ ያሉ ሆነው መስፋት የሚፈልጉትን የስራ ፈጣሪዎች ያሳትፋል። ውድድሩ የገንዘብ ፣ ስልጠና ፣ የስምምነት ወይም ከአገር ውስጥና ከአለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ጋር የግንኙነት እድሎችን ይሰጣል።

ድረ-ገፅ