እስከ 2012/2013 ሊኖር የሚችለውየኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሁኔታ


ጠቅላለ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት ትንበያ (ለ2011/2012)

ገንዘብ ሚኒስቴር

11%

አለም ባንክ

9%

አይ.ኤም.ኤፍ

8.5%

አፍሪካ ልማት ባንክ

7.8%

የአይ.ኤም.ኤፍ ሪፖርት ስለኢትዮጵያ (2012)

በቀደመዉ አመት የተከሰተዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት ስለሚሰክን፤ የገንዘብ ፍሰት ስለሚጨም እና የውጭ ጫናን ስለሚቀንስ በ2011/2012 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ8.5% እንደሚያድግ ይጠበቃል፡፡ ሀገሪቱ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ስጋት እንደሚኖርባት የዕዳ ጫና ግምገማዎች ያመለክታሉ፡፡ የሀገሪቱን ቁልፍ የኢከኖሚ ዘርፎች ወደ ግል ይዞታ ለማዛወር እንዲሁም ለውድድር እና ግል ኢንቨስትመንት ክፍት ለማድረግ በዓመራሩ የተጀመረዉ የሪፎርም እርምጃ ለኢከኖሚው ጠንከራ የእድገት አቅም ሊያጎናጽፍ ይችላል፡፡

 

ሙሉ ሪፖርት

አፍሪካ ልማት ባንከ የአፍሪካ ልማት ትንበያ (2010)

የእንዱስትሪ እና አገልግሎት ዘርፎች የበለጠ እንደሚስፋፉ ይጠበቃል፤ እንዲሁም ግብርናው ሰለሚያገግም የኢትዮጵያ ጠቅላላ ያገር ውስጥ ምርት በ2017/2018 ከነበረው 7.7% በ2011/12 እና 2012 ወደ 8.2% እንደሚያድግ ይገመታል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ለኢንዱስትሪው ዘርፍ እድገት ዋናው አንቀሳቃሽ ሞተር የሚሆን ሲሆን በማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር፣ መስኖ ልማት እና መሰል ግብዓቶች ላይ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ደግሞ ለግብርናው ዘርፍ መነቃቃት ዋናውን ሚና ይጫወታል፡፡ የመንግስት ኢንቨስትመንት መቀዛቀዝ አዝማሚያ አንደሚቀጥል የሚጠበቅ ሲሆን ለዚህም ዋናው ምክንያት መንግስት የብድርን ጫና ለመቀነስ የሚያደርገው ጥንቃቄ ነው፡፡ በመንግስት እንደተገለፀው የባቡር መስመሮች፣ የመርከብ ድርጅት፣ የአየር መንገድ፣ የሎጂስቲክስ፣ የኃይል ማመንጫ፣ የቴሌኮሚኒኬሽን ተቋማት ወደ ግል ይዞታ ሲዛወሩ የግል ኢንቨስትመንትን ከማሳደጉም በላይ የመንግስት ልማት ወጪን የመቀዛቀዝ አዝማሚያ እንደሚያነቃቃው ይጠበቃል፡፡

 

 

ሙሉ ሪፖርት

የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ ማጠቃሻ አጋዥ መጽሃፍ ሴፊየስ ጥናት እና ትንተና


ስለኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ በሚወሳበት ጊዜ ኢንቬስተሮች የሚጠይቋቸውን 10 ዋናዋና ጥያቄዎችን በማንሳት እና ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ በማቅረብ ስለሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ ግንዛቤ ይፈጥራል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያን የ10 ዓመት ተጨባጭ የገንዘብ ፣ የበጀት እና የውጭ ሴክተር መረጃዎችን እንዲሁም ስለኢኮኖሚው የወደፊት አዝማሚያ ትንበያ ያቀርባል፡፡

 

ሙሉ ሪፖርት