ማበልጸጊያዎች


ስራ መጀመር እንደትችሉ ሊረዷችሁ የሚችሉ አቃፊ ተቋሞች አዲስ አበባ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ ድረ-ገጾቻቸውን ጎብኙ፡፡

አይ.ሲ.ቲ.ፓርክ

200 ሄክታር ላይ ያረፈዉ አይ.ሲ.ቲ. ፓርክ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀርባ ይገኛል፡፡ የመሥሪያ ቦታን ጨምሮ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት፣ በቂ የኤሌክትሪከ ኃይል አቅርቦት፣ አስተማማኝ የዳታ ደህንነት፣ መሬት በተመጣጣኝ ዋጋ እና ተያያዥ አገልግሎቶችን በተጨማሪም የተለያዩ ማበረታቻዎችን ያቀርባል፡፡ የገንዘብና የፋይናንስ አገልግሎቶችን ጨምሮ የአንድ መስኮት የመንግስት አገልግሎቶች የሚሠጡ ተቋማት ይገኛሉ፡፡ እስከአሁን ከ70 በላይ የኢ.ኮ.ቴ ኩባንያዎች ወደ ፓርኩ ገብተዋል፡፡

አይስ አዲስ

በ2011 የተቋቋመው አይስ አዲስ ለጀማሪ የኢ.ኮ.ቴ ድርጅቶች ስልጠና እና የጋራ መስሪያ ቦታ ያማቻቻል፡፡

ድረ-ገፅ

ብሉ ሙን

ብሉ ሙን በ2017 የተመሠረተ አቃፊ ሲሆን በዓመት ሁለት ጊዜ በሚያደርገው አገር ዓቀፍ ውድድር የሚደግፋቸውን ጀማሪ ድርጅቶችን ይመርጣል፡፡ የተመረጡ ጀማሪዎች ስልጠና፣ የቢዝነስ ማበልጸፀጊያ ድጋፍ፣ የመሥሪያ ቦታ፣ እና የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ ይመቻችላቸዋል፡፡

ድረ-ገፅ

ዘ ኤስክ ሀብ

በአፍሪካ የአመራር ጥናት ማዕከል በ2014 የተጀመረው ይህ አቃፊ ድርጅት ጀማሪ ድርጅቶች ኃሳባቸውን ወደ ተጨባጭ ቢዝነሶችና አገልግሎቶች እንዲያሸጋግሩ ያማክራል፣ ይድግፋል ፡፡ ይኼንንም ለማሳካት የሥልጠና እና የጋራ መስሪያ ቦታ ያቀርባል፡፡

ድረ-ገፅ