የኢንዱስትሪፓርኮች


ያለቁ የኢንዱስትሪ ፓርኮች
በኮንስትራክሽን ላይ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች

ሁሉም ኢንዱስትሪፓርኮች


ኢትዮጵያ ከግብርና መሪ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መሪ ኢኮኖሚ ለመሸጋገር እንዲሁም የአፍሪካ የአምራች ኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ቁልፍ ፕሮጄክቶች ናቸው፡፡በተጨማሪም መንግስት በነዚህ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አማካኝነት ወደ 200,000 ቀጥተኛ እና 500,000 ቀጥተኛ ያልሆኑ የሥራ ዕድሎች ለመፍጠር አቅዷል፡፡በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የማምረቻ ፋብሪካዎችን ለሚገነቡ የግል ባለሃብቶች የግብር እፎይታ፣ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማግኘትና ለማከናወን ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎቶች፣ የአንድ መስኮት አገልግለቶች እና ሌሎች ማበረታቻዎች ይቀርባሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ፓርኮች በቀላል ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሆነው የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባትና ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ይቆጣጠራል፡፡ እስከ 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሥራ ገብተዋል ፡፡ለአካባቢ ተስማሚ ሆኖ የተገነባውና ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች የተማሉለት የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ካሉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ተጠቃሽ ነው፡፡ ግንባታው ሰኔ 2009 ተጠናቆ ወደ ሥራ የገባው ይህ የኢንዱስትሪ ፓርክ እንደ ፒ.ቪ.ኤች ያሉ 18 በዓለም ታዋቂ የአልባሳትና ጨርቃጨርቅ ኩባኒያዎችን መሳብ ችሏል፡፡

ትግራይ አማራ አፋር ድሬዳዋ ሃረር ሶማሊያ ኦሮሚያ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋምቤላ አዲስ አበባ ቤንሻንጉል-ጉምዝ አሶሳ ኢ . ጅማ ኢ . ቡሬ ኢ . ይርጋለም ኢ . ሃዋሳ ኢ. ቡልቡላ አ.. አዳማ ኢ. ቦሌ ኢ . ቂሊንጦ ኢ . Huenjaan አርቲ ኢ . CCECC- አርቲ ደብረብርሃን ኢ . ቢሾፍቱ ኢ . ሞጆ ቆዳ ፓርክ ኢስተርን ኢንዱስትሪአል ፓርክ ድሬዳዋ ኢ . CCECC- ድሬዳዋ አይሻ ኢ . ኮምቦልቻ ኢ . ባህርዳር ኢ . Hop L un ltd ሰመራ ኢ . መቀሌ ዲ ቢ ኤል ቬሎሲቲ ሃመር አ.. በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሸን የተገነቡ የግል ኢንዱስትሪአል ፓርክ አግሮ ኢንዱስትሪአል ፓርክ

የመንግሥት ኢንዱስትሪ ፓርኮች


ወደስራ የገቡ ኢንዱስትሪ ፓርኮች

ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት ቦታ ዘርፍ ስፋት አስተያየት
ቦሌ ለሚ ምዕራፍ 1 ደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች 174 ሄ ከቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቅርብ ርቀት ያለ
ሀዋሳ ምዕራፍ 1 ደቡብ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ በ275 ኪ.ሜ ርቀት ጨርቃጨርቅና አልባሳት 300 ሄ ፒቪ.ኤች ፣ ጄፒ ጨርቃ ጨርቅ እና አርቪንድ የመሳሰሉ ታዋቂ ኩባኒያዎች ገብተዋል
መቀሌ ሰሜን ኢትዮጵያ ከመቀሌ በ5 ኪ.ሜ ርቀት ጨርቃጨርቅና አልባሳት 75 ሄ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ለሆነው ያሰብ ወደብ በቅርብ ርቀት ይገኛል
ጂማ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅና አልባሳት ምዕራፍ 1 75 ሄ / በአጠቃላይ 150 ሄ -
አዳማ ከአዲስ አበባ በ75 ኪ.ሜ. ርቀት ጨርቃጨርቅና አልባሳት ማሽንና መሣሪያዎች 120 ሄ ከአ.አ.-ጅቡቲ ባቡር መስመር እንዲሁም አዲስ አበባ - አዳማ የፍጥነት መንገድ መስመር ላይ ይገኛል
ኮምቦልቻ ከኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ በ 6 ኪ.ሜ ርቀት ጨርቃጨርቅና አልባሳት ምዕራፍ 1 75 ሄ -
ድሬደዋ ምስራቅ ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ወደብ በ318 ኪ.ሜ ርቀት ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ተሸከርካሪ መገጣጠም፣ ኤሌክትሮኒኪስ፣ ምግብ ማቀነባበር፣ ወረቀትና ተያያዥ ምርቶች እና ኬሚካል፡፡ 150 ሄ ይህ እንዱስትሪ ፓርክ ኢትዮጵያ ለውጭ ገቢ ንግድ በዋነኛነት ከምትጠቀምበት የጅቡቲ ወደብ በቅርብ ርቀት ይገኛል፡፡
ቂሊንጦ አዲስ አበባ መድሃኒት 279 ሄ ፓርኩ መሰረተልማቱ የተሟላ መሬት ያቀርባል፡፡ ባለሃብቶች የራሳቸውን የማምረቻ ሼድ ይገነባሉ፡፡ የሊዝ ዋጋ በዓመት 3.59 ዶላር በካሬ ሜትር ለ 40 ዓመት፡፡
ቦሌ ለሚ II አዲስ አበባ ጨርቃጨርቅና አልባሳት ቆዳና የቆዳ ውጤቶች 171 ሄ የሊዝ ዋጋ በዓመት 3.31 ዶላር በካሬ ሜትር ለ 40 ዓመት
ደብረ ብርሃን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከአ.አ. በ110 ኪ.ሜ ርቀት ጨርቃጨርቅና አልባሳት የግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያ 75 ሄ -

በግንባታ ላይ ያሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች

ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለበት ቦታ ዘርፍ ስፋት አስተያየት

የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርክ


ገትማ ገትማ ገትማ ገትማ ገትማ የተግዉማፓ ገትማ ገትማ ገትማ
ገትማ:- የገጠር ትራንስፎርሜሽን ማዕከል
የተግዉማፓ:- ተቀናጀ የግብርና ዉጤቶች ማቀነባበሪያ ፓርክ

ኢትዮጵያ በዩኒዶ ድጋፍ 17 የተቀናጀ ግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የመገንባት እቅድ አላት፡፡ በመጀመሪያ ምዕራፍ የአራቱ ፓርኮች ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ እነዚህ የግብርና ውጤት ማቀነባበሪያ ፓርኮች ሀገሪቱ በግብርና ምርቶች ላይ እሴት ለመጨመር የምታደርገውን ጥረት የሚደግፉ ናቸው፡፡

የግብርና ውጤት ማቀነባበሪያ ፓርኮች ልቅ/ግልጽ የማምረቻ ዞኖች፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማምረቻ አካባቢዎች፣ ግብዓቶች ተመጥነው የሚለቀቁበት ቴክኖሎጂን ያካተቱ ዘመናዊ የግብርና ማሳዎች፣ የዕውቀትና የምርምር ማዕከሎች፣ የገጠር ማዕከሎች፣ የግብርና መሠረተልማቶች፣ የምርት ማሳሰቢያ ጣቢያዎች፣ የመጀመሪያ ደረጃ ማቀነባበሪያ ማዕከሎች፣ የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት እና የግብርና ምርቶች ሽያጭ መሠረተልማቶች እነዲኖራቸው ይደረጋል፡፡

በነዚህ የግብርና ውጤት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 100 ኪ.ሜ. ዙሪያ እንደ ምርት ማሰባሰቢያ ጣቢያ ሁነው የሚያገለግሉ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ማዕከላት ይገነባሉ፡፡ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ማዕከላት መጋዘኖች፣ የግብዓት አቅርቦት፣ የማበጠሪያ፣ ደረጃ ማውጫ፣ የኤክስቴሽን አገልግሎት፣ የቅድመ-ማቀነባበር ሥራዎች እና የአነስተኛ ብድር አገልግሎቶች እንዲያቀርቡ ይደረጋል፡፡

ምዕራፍ I የተቀናጀ የግብርና ውጤት ማቀነባበሪ ኢንዱስትሪ ፓርኮች


የፓርኩ ስም የምርት ዓይነት ስፋት በሄክታር
ቡልቡላ ስንዴ፣ ገብስ፣ ቦለቄ፣ ባቄላ፣ ቲማቲም፣ ድንች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የወተት ተዋጽኦ፣ አሳ፣ የዶሮ ተዋጽኦ፣ ማር እና ስጋ 263
በአከር ዘንጋዳና ሰሊጥ ፣ አትክልትና ፍራፍሬ የወተት ተዋጽኦ ፣ ስጋ ፣ እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች 151
ቡሬ ዘንጋዳና ሰሊጥ ፣ አትክልትና ፍራፍሬ የወተት ተዋጽኦ ፣ ስጋ ፣ እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች 155
ይርጋለም ጥራጥሬ፣ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የወተት ተዋጽኦ፣ ስጋና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦ 101

ፋይናንስ


በየአመቱ በአማካይ የ28% የተቀማጭ ገንዘብ እና 31% የብድር አቅርቦት እድገት ያሳየዉ የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ባለፉት አስርተ ዓመታት ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ የመጣ ዘርፍ ነው፡፡