ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ያደረጋት፡-


ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ጽኑ አቋም ያለው አመራር

መንግስት አጠቃላይ መረጋጋት እንዲኖር እና የሕዝብ ተሳትፎ ለማሳደግ መጠነ-ሰፊ የሪፎርም እርምጃዎችን እየወሠደ ነው፡
የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ እንደ ቴሌኮሙኒኬሽን ፣ ኤሌክትሪሲቲ፣ አየርመንገድ ያሉ ቁልፍ ተቋማትን ለግል ዘርፍ ተሳትፎ ክፍት ለማድረግ መንግስት ወስኗል፡፡
መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ የቢዝነስ ስራ ቀላል እንዲሆን ማድረግን ዋና የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ለዚህም ዋናው አቀንቃኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው፡፡
አስከ ላይኛው አመራር ለኢንቨስትመንት መስፋፋት ቁርጠኝነት አለው ፡፡
እንደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ መጠና ሰፊ ፕሮጄክቶች እና ማበረታቻዎች እንዲሁም ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች እየተገነቡ ነው፡፡
ለስትራቴጂካዊ ዘርፎችና ኤክስፖርት ተኮር ኢንቨስትመንቶች የተለያዩ ዓይነት የማበረታቻ ፓኬጆች ይሰጣሉ፡፡

ለኢንቨስትመንት የተመቸ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ

ኢኮኖሚው በጥቅሉ፤የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ2007 እስከ 2016/17 በነበሩት አስርተ ዓመታት በአማካይ 10.3% በማደግ ጠንካራና መሠረተ ሰፊ እድገት አሳይቷል፡፡ (የአለም ባንክ ሪፖርት)
ኢትዮጵያ ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ግንባር ቀደም ከሆኑ ሀገሮች ውስጥ አንዷ ናት፡፡ (በ2017/2018 4 ቢሊዮን ዶላር እንቨስትመንት ለመሳብ ችላለች)
መሠረተ ልማት፤በቅርቡ የተጠናቀቀው የአዲስ አበባ ጂቡቲ የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ማዕከላት ከጂቡቲ ወደብ ጋር አስተሳስሯል፡፡
በአፍሪካ ግንባር ቀደም የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 100 በላይ መዳረሻዎች የሚበር ሲሆን የዚሁ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎት ወደ 36 አለምዓቀፍ የጭነት መዳረሻዎች የበረራ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም 20 የአገር ውስጥ በረራ መዳረሻዎች አሉት፡፡
እንደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ መጠና ሰፊ ፕሮጄክቶች እና ማበረታቻዎች እንዲሁም ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች እየተገነቡ ነው፡፡
ለስትራቴጂካዊ ዘርፎችና ኤክስፖርት ተኮር ኢንቨስትመንቶች የተለያዩ ዓይነት የማበረታቻ ፓኬጆች ይሰጣሉ፡፡
የውሃ ሃይል ማመንጫ፣ ነፋስና፣ ጆተርማልን ጨምሮ ሰፊ የተዳሽ ሃይል ኢንቨስትመንት ገበያ አለ፡፡ በተጨማሪም 6000 ሜጋ ዋት የሚያመነጨውና በአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ ግድብ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በግንባታ ላይ ይገኛል፡፡
58 ሚሊዮን የሞባይል ተጠቃሚዎች ያሉት እያደገ የመጣው ሰፊ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ገበያ (2016/2017)

ተስማሚ የገበያ ሁኔታዎች

ለመካከለኛው ምስራቅ፣ ለአውሮፓና ኤዥያ ቅርበት ያለው ስትራቴጂካዊ ቦታ
በቀላሉ ሰልጥኖ በተመጣጣኝ ደሞዝ ለሥራ ዝግጁ ሊሆን የሚችል 59 ሚሊዮን ሠራተኛ ኃይል
በአጎአ (AGOA) እና ኢ.ቢ.ኤ (EBA) አማካኝነት ከቀርጥና ከኮታ ነፃ ገበያ በአሜሪካ እና በአውሮፓ
ከኢትዮጵያ ወደ ጃፓን፣ ካናዳ፣ ቻይና፣ ቱርክ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ ከኮታና ቀረጥ ነፃ ገበያ፡፡
ኢትዮጵያ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ (COMESA) አባል በመሆኗ ባላት የልዩ ተጠቃሚነት መብት 400 ሚሊዮን የሚሆነው የማህበሩ አባል ሃገራት ህዝብ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገበያ እድል ያስገኝላታል፡፡
የአፍሪካን አህጉራዊ የነፃ ገበያ ስምምነትን በመፈረም አጽድቃለች፡፡