ፕሮጀክቶች


የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ማዕክል

ኢ.ዲ.ሲ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት መርሃግብር ጋር በመተባበር የሚከወን ከፊል መንግስታዊ የሆነ የማማከር እና ስልጠና መርሃ ግብር ነዉ፡፡ዋና ጽ/ቤቱ አዲስ አበባ ሲሆን ቢሾፍቱ፣ ሃዋሳ፣ ባህርዳር እና መቀሌ ቅርንጫፎች አሉት፡፡
የሚሰጣቸዉ አግልግሎቶችለጀማሪ ኢንተርፕረነሮች በተለይም ለወጣቶች የኢንተርፕረነርሽፕ እና የንግድ ስራ ስልጠና
በተመረጡ ዪኒቨርሲቲዎች ዉስጥ የኢንተርፕረነርሽፕ ልቀት ማዕከሎችን መክፈት
በተለይ ሴቶችና ወጣቶች ላቀቋቋሟቸዉ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተከታታይ የምክር ድጋፍ መስጠት
የኢንተርፕረነርሸፕ ስልጠና ዎርክሾፕ መስጠት፡፡ (Enterpreneurship Training Workshop-ETW) በተባበሩት መንግስታት የንግድ እና ልማት ጉባኤ (UNCTAD) የተዘጋጀ ሰልጣኞችን የማከለ እና በአለምአቀፍ ደረጃ እዉቅና ያለዉ የስድስት ቀን ስልጠና ነዉ፡፡

ለበለጠ መረጃ እዚህ ግባ


የሴቶች ኢነተርፕሬነርሽፕ ልማት መርሃግብር

ትኩረት : በከፊል ወይም በሙሉ በሴቶች ባለቤትነት ለተቋቋሙ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
የተመደበ የገንዘብ መጠን : 50 ሚሊዮን ዶላር
የፕሮጄክት ዘመን: ከ2005-2012 መጨረሻ
የሚሰጠዉ ድጋፍ አይነት: የገንዘብ ድጋፍ
ፈጻሚ ተቋማት: የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ፌደራል የከተማ ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር

ለበለጠ መረጃ እዚህ ግባ


ኢንተርፕራይዝ ፓርትነርስ

ኢንተርፕራይዝ ፓርትነርስ የኢንግሊዝ መንግስት አለምዓቀፍ የልማት ድርጅት (ዲ.ኤፍ.አይ.ዲ) ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚተገብረዉ የግል ዘርፍ ኢንተርፕራይዝ ልማት መርሃግብር አንኳር ክፍል ነዉ፡፡ ለዚህ መርሃግብር ማስፈጸሚያ ዩኬኢድ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ዲ.ኤ.አይ ፣ ፈርስት ኮንሰልት፣ ኢ.ታድ ፣ ኢንክሉድ እና ቢ.ሲ.ኤ.ዲ የተባሉ ድርጅቶች ደግሞ ተባባሪ ፈጻሚዎች ናቸዉ፡፡የኢንተርፕራይዝ ፓርትነርስ ስራ በሁለት ዋናዋና አምዶች ላይ የተመሠረተ ነዉ፤የግብርና ዉጤቶች ማቀነባበር-መንግስት ትኩረት ላደረገባቸዉ ሶስት ዘርፎች ማለትም የአልባሳት፣ ቆዳ እና የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፎችን የገብያ ሥርዓት ማጠናከር፡፡
የፋይናስ ተደራሽነት - ወደ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ትላልቅ ኢንተርፕራይዞች የሚደረገዉን የመዋዕለንዋይ ፍሰት መጠን መጨመር እና በመስኩ ቀጥተኛ የዉጪ ኢንቨስትመንት ማበረታታት፡፡የኢንተርፕራይዝ ፓርትነርስ ግብ 45,000 የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር (75% ለሴቶች) እንዲሁም የ65,000 ደሃ ቤተሰቦችን ገቢ በማሳደግ ዘላቂ ለዉጥ ማምጣት ነዉ፡፡

ለበለጠ መረጃ እዚህ ግባ


የሴቶች እና ወጣቶች መተዳደሪያ ማሻሻያ ፕሮጄክት

በስዊድን አለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ሲዳ) የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወነዉ የሴቶች እና ወጣቶች መተዳደሪያ ማሻሻያ ፕሮጄክት አዲስ አበባ ዉስጥ ላሉ ወጣቶች እና ሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ፕሮጄክት ነዉ፡፡የፕሮጄክቱ ዋና ከዋኝ የሆነዉ ኤሰ.ኤን.ቪ በቀጣዮቹ አምስት አመታት በተለይ የሴቶችንና ወጣቶችን ገቢ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማሳደግ የ200,000 ሰዎችን ኑሮ ለማሻሻል እየወራ ይገኛል፡፡.የፕሮጄክቱ ዓላማዎች፡ስለ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታ የተሸለ ግንዛቤ እንዲኖር ጥናት ማድረግ፣
ሴቶችን እና ወጣቶችን የበለጠ ሊያስትፉ የሚችሉ የኢኮኖሚ መስኮችን መለየት እና በነዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ፣
ሴቶች እና ወጣቶች በአንድአንድ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተሳታፊ እንዳይሆኑ የሚያቅቡ ተግዳሮቶችን መለየት ዘላቂ ለዉጥ ማምጣት ነዉ፡፡

ለበለጠ መረጃ እዚህ ግባ


የሴቶች እና ወጣቶች መተዳደሪያ ማሻሻያ ፕሮጄክት

በስዊድን አለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ሲዳ) የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወነዉ የሴቶች እና ወጣቶች መተዳደሪያ ማሻሻያ ፕሮጄክት አዲስ አበባ ዉስጥ ላሉ ወጣቶች እና ሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ፕሮጄክት ነዉ፡፡የፕሮጄክቱ ዋና ከዋኝ የሆነዉ ኤሰ.ኤን.ቪ በቀጣዮቹ አምስት አመታት በተለይ የሴቶችንና ወጣቶችን ገቢ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማሳደግ የ200,000 ሰዎችን ኑሮ ለማሻሻል እየወራ ይገኛል፡፡.የፕሮጄክቱ ዓላማዎች፡ስለ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታ የተሸለ ግንዛቤ እንዲኖር ጥናት ማድረግ፣
ሴቶችን እና ወጣቶችን የበለጠ ሊያስትፉ የሚችሉ የኢኮኖሚ መስኮችን መለየት እና በነዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ፣
ሴቶች እና ወጣቶች በአንድአንድ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተሳታፊ እንዳይሆኑ የሚያቅቡ ተግዳሮቶችን መለየት ዘላቂ ለዉጥ ማምጣት ነዉ፡፡

ለበለጠ መረጃ እዚህ ግባ


ብሪቲሽ ካዉንስል-ማህበራዊ ኢንተርፕራይዝ ፕሮጄክት

ይህ ፕሮጄክት የሶስት አመት ፕሮጄክት ሲሆን በ 28 አገሮች በመከናወን ላይ ያለ የብሪትሽ ካዉንስል የአለም ማህበራዊ ኢንተርፕራይዝ መርሃግብር አንድ ክፍል ነዉ፡፡ መርሃግብሩ ማህበራዊ ኢንተርፕራይዝ ፕሮጄክቶችን በመደገፍ ማህበራዊ እና የተፈጥሮ አካባቢ ችግሮችን በመቅረፍ የማህበረሰቡን ኑሮ በማሻሻል ላይ በማተኮር ይሰራል፡፡ ፕሮጄክቱ መልካም የማህበረሠብ ለዉጥ፣ አካታች እድገት እና ዘላቂ ልማት እንዲስፋፋ ይተጋል፤ ይህም ስራዉ በእንግሊዝ እና በሌሎች ሀገሮች መሃክል ያለዉ የተራድኦ ግኑኝነት በመማማር እና በመተማመን ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ይጥራል፡፡በተጨማሪም ለኢንተርፕሬነሮች ስልጠና፣ ምክር እና የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡በትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርስቲዎች የማህበራዊ ኢንተርፕራይዝ ትምህርት እንዲስፋፋ ድጋፍ ያደርጋል፤
የፖሊሲ ዉይይቶችን ያዘጋጃል፤
ጥናት በማድረግ የጥናት ገኝቶች ማሰራጫ መድረኮችን ያመቻቻልለበለጠ መረጃ እዚህ ግባ

ለበለጠ መረጃ እዚህ ግባ


ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ኢንተርፕረነርሽፕ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት መርሃግብር

ሲድ የቢዝነስ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ ኢንተርፕረነሮች፣ ጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ የስራ ሃሳብ እነዲያመነጩና እንዲተገብሩ የቴክኒክ ደጋፍ ይሰጣል፤ የቢዝነስ ልማት አገልግሎቶች አና አዳዲስ የገንዘብ ምንጮች እንዲስፋፉ ድጋፍ ያቀርባል፡፡ በተጨማሪም የነዚህ ድርጅቶች የገንዘብ አያያዝ እዉቀት እና አስተዳደር እንዲበለጽግ ድጋፍ ይሰጣል፡፡የሲድ ፕሮጄክት የትኩረት መስኮች የሚከተሉት ናቸዉ:የገንዘብና ገንዘብ-ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶች አቅርቦት፣ ጥራት እና ተደራሽነትን ማሻሻል
ጥቃቅን አነስተኛና መሃከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ከነዚህ አገልግሎቶች ጋር ማገናኘት
አገልግሎት አቅራቢዎችን በየዘርፉ ከሚታወቁ ድርጅቶች ጋር ማስተሳሰር
የግሉ ዘርፍ ወደ መደበኛ አሰራር እንዲሸጋገር መደገፍ
ኢትዮጵያ ዉስጥ ስራ ለመስራት የተመቹ ከባቢያዊ የፖሊሲ መሠረቶች እንዲኖሩ ማህበራት አትኩረዉ እንዲሰሩ የአቅም ድጋፍ ማድረግ፡፡

ለበለጠ መረጃ እዚህ ግባ