ድጋፍ


የኢኖቬሽንና ሳይንስ ሚኒስቴር

የሚኒስቴሩ ተግባር፡ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን መስክ የሰብዓዊ ኃብት ልማት እቅድ ማዘጋጀትና ማከናወን ሲሆን ለዚህም ከሚመለከታቸው አካለት ጋር ትብብር ይፈጥራል፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቪሽን እድገት አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሽልማትና ማበረታቻ የሚሰጥበትን ስርዓር ይዘረጋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
የአይ.ሲ.ቲ. ጳክ

ይህ 200 ሄክታር ላይ ያረፈ ፓርክ አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከቦሌ አለምዓቀፍ አየር ማረፊያ በስተጀርባ ይገኛል፡፡ የመስሪያ ቦታን ጨምሮ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግለት፣ በቂ የኤሌክትሪከ ኃይል አቅርቦት፣ አስተማማኝ የዳታ ደህንነት፣ መሬት በተመጣጣኝ ዋጋ፣ ተያያዥ አገልግሎቶችን እንዲሁም የተለያዩ ማበረታቻዎችን ያቀርባል፡፡ የባንክና የገንዘብ ድጋፍ አገልግሎቶችን ጨምሮ የአንድ መስኮት የመንግስት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ እስከአሁን ከ70 በላይ የኢ.ኮ.ቴ ኩባኒያዎች ወደ ፓርኩ ገብተዋል፡፡

የኢኖቬሽን ሽልማት እና ለጥናት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ

በ2009 የተጀመረው ብሔራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሸልማት እስከአሁን ለ1500 የፈጠራ ስራዎች/የፈጠራ ሰዎች ሽልማት ሰጥቷል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ እዚህ ግባ

ለስራ ፈጣሪዎች ወይም የስራ ፈጣሪ ቡድን መንግስት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ድጋፎች ይሰጣል፡፡ የነዚህ አገልግሎቶች/ድጋፎች አቅርቦትና አሰጣጥ እንደየሁኔታው ሊለያይ ይችላል፡፡የሚሠጡ ድጋፎች፤የገንዘብ ድጋፍ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት አማካኝነት
ስለ ለስራ ፈጣሪዎች እና ወሳኝ የንግድ ስራ ክህሎቶች ስልጠና
የማምረቻ እና ሽያጭ ቦታዎች ወይም ሼዶች
መሬት ለሚያስፈልጋቸው ፕሮጄክችቶ መሬት (ካለው ወረፋ ይህ አገልግሎት ሊዘገይ ይችላል)
በኤግዚቢሺን እና በኢንተርፐራይዝ ባለቤቶች በውል በሚተዳደሩ ሱቆች አማካኝነት የገበያ ትስስር፡፡