ቡድን


ዳይሬክተር

አለምጸሃይ ደርሶልኝ ለገሰአዳዲስ የሥራ ዕድል ፈጠራና ፕሮጄክቶች ዳይሬክቶሬት


ወይዘሮ አለምጸሃይ ደርሶልኝ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን አዳዲስ የሥራ ዕድል ፕሮጄክቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸዉ፡፡ ወደዚህ ኃላፊነታቸዉ ከመምጣታቸዉ በፊት በአጋር ኢትዮጵያ በጎአድራጎት ድርጅት የሙያ ስልጠና አማካሪ ሆነዉ የሠሩ ሲሆን በተጨማሪም በራስ አገዝ ሴቶች ድርጅት (ራሴድ) በቡድን መሪነት ሰርተዋል፡፡ ቀደም ብሎም በፌደራል የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንተርፕሬነርሽፕ ትምህርት ቡድን መሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡

ወይዘሮ አለምጸሃይ በማርኬቲንግ እና ማኔጅመንት ከጅማ ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ከሊድስታር ዩንቨርስቲ ደግሞ በፕሮጄክት አመራር እና ቢዝነስ አስተዳደር የማስተርስ ዲግሪ አግንተዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ ዓለምአቀፍ የትምህርት ተቋማት በአመራር እና ቢዝነስ አስተዳደር የተለያዩ የሰርቲፊከት ስልጠናዎችን ወስደዋል፡፡