የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን የፌዴራል መንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት የተቋቋመ ሲሆን የኮሚሽኑን ተግባር፣ ኃላፊነት እንዲሁም አደረጃጀት ለመወሰን በሚኒስትሮች ምክር ቤት በጸደቀው ደንብ ቁጥር 435/2011 ብሔራዊ የስራ ፈጠራ አጀንዳውን ለመምራት፣ ባለድርሻ አካላትን ለማቀናጀት እንዲሁም አፈጻጸምን ለመከታተል እና ለመደገፍ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

የአገሪቱን የስራ ዕድል ፈጠራ በአዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦች፣ በቅንጅት እና በተግባር መምራት

ኢትዮጵያ ሁሉም ዜጋ ዘላቂ ስራ የሚያገኝባት አገር ሆና ማየት

ፈጠራ
ልህቀት
ትብብር
ባለቤትነት

የኮሚሽኑ መዋቅር


Commissioners

ባልደረቦች


ኮሚሽነር

አቶ ንጉሡ ጥላሁን ገ/አማኑኤል


አቶ ንጉሱ ጥላሁን የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሲሆኑ ፣ ወደዚህ የስራ መደብ ከመምጣታቸው በፊት የኢ/ፌ/ዲ/ሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት መሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡

በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከማስተማር ጀምሮ እስከ አማራ ክልል ትምህርት ቢሮ መሪነት ድረስ በሰፊው ትምህርት ተኮር የሆነ የካበተ ልምድ ያላቸው ሲሆን በተጨማሪም በአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነውም አገልግለዋል ፡፡

አቶ ንጉሱ በቅርብ ጊዚያት የመንግስት ሰራተኛ እና በከፍተኛ የመንግስት አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

ቀደም ሲል የአማራ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የቀድሞው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት ኮሚሽነር በበረካታ የመንግስትና የአስተዳደር ቦታዎች ላይ የሰሩ ሲሆን የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽንን ከመምራት ባሻገር በስራ በአስፈፃሚነት ሚና ፡ በትምህርት ተቋማት እና በመገናኛ ብዙሃን ውስጥ የቦርድ አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ ፡፡